እናመሰግናለን! -የአሥራት ሚድያ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ።

የአሥራት ሚድያ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ያደረጋቸውን የዕርዳታ ጥሪዎች በመቀበል፤ ለተቋሙ የፋይናንስ ችግር መፍትሔ አጋዥ ይሆን ዘንድ የካሊፎርኒያ አማራ ማኅበር በሳንዲያጎ፣ የሎስ አንጀለስ የአማራ ማህበር፣ የዲሲና የአካባቢዋ አማራ ማኅበር እና የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ (ኦሃዮ) ለአሥራት ሚድያ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። ለተቋሙ ጊዜያዊ ችግሮች ይደርስ ዘንድ ላደረጉት ድጋፍ በሕዝባችን ስም እያመሰግንን። ተቋሙን በዘላቂነትና አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለማስቀጠል፣ ብሎም ለማጎልበት፣ ሌሎች ማኅበራት፣ እንዲሁም የተደራጃችሁና ያልተደራጃችሁ የማኅበረሰባችን አባላት በወርኃዊ ክፍያ መልክ ድጋፋችሁን ታደርጉ ዘንድ በሕዝባችን ስም እንጠይቃለን።
የአሥራት ቤተሰቦችንና ደጋፊዎችን ጥያቄዎች ለመመለስ እየሰራናቸው ያሉ ሌሎች ተግባራት እንደተጠበቁ ሆነው፤ የአሥራት ሚድያ የኢንተርኔት ገጽ (https:/www.asratmediahouse.org) በአዲስ ቅርጽና ይዘት ሥራ መጀመሩን ስናበስር በደስታ ነው።
በምታደርጉት ሁሉን አቀፍ ድጋፍና አስተያየት ተቋሙንና የተቋሙን ሁለንተናዊ ገጽታ ልናሻሽል እንደምንሰራ ቃል እየገባን፣ የማገልገል ዕድሉን በማግኘታችን ታላቅ የክብር ስሜት እንደሚሰማን ልንገልጽ እንወዳለን።
ድር ቢያብር፤ አንበሳ ያስር!
አሥራትን መደገፍ፣ እውነትን፣ ፍትህንና ዲሞክራሲን መደገፍ ነው!
የአሥራት ሚድያ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *