የአሥራት ሚድያ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በሕዝባዊ ውይይቶች መሳተፉን እንደቀጠለ ነው

የአሥራት ሚድያ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በሕዝባዊ ውይይቶች መሳተፉን እንደቀጠለ ነው። የተለያዩ የአማራ ሲቪክ ማኅበራት በጠሯቸው ዓለማቀፍ የስልክ ስብሰባዎች (ቴሌኮንፈረንሶች) ላይ የአሥራት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት በመገኘት ከአሥራት ሚድያ ቤተሰቦችና ወዳጆች ጋር ተወያይተዋል።
የውይይት መድረኮቹ የተዘጋጁት በአማራ ማህበር በኔቫዳ ማክሰኞ ሚያዝያ ፳ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. (28 April 2020)፤ እንዲሁም በሞገድ ዐማራ ቀስቃሾች ስብስብ (ሞዐቀስ) ቅዳሜ ሚያዝያ ፳፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. (02 May 2020) ነበር።
የስልክ ስብሰባዎቹ እያንዳንዳቸው ለሰዓታት የተደረጉ ሲሆን፤ ከተቋሙ ጋር በተያያዙ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሥራ አስፈጻሚ ቦርዱ አባላት ማብራሪያና መልሶች ሰጥተዋል። ውይይቶቹ ከፍተኛ ተነሳሽነትና ተቆርቋሪነት የታየባቸው ነበሩ።
በቅርቡም የአሥራት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ እሁድ መጋቢት ፳፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. (05 April 2020) ረዘም ያለ ዓለማቀፍ የስልክ ውይይት አድርጎ በርካታ ሃሳቦችን ማድመጡ፤ ማብራሪያ መስጠቱና ጥያቄዎችን መመለሱ ይታወሳል።
የአሥራት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ውይይቶቹን ላዘጋጁት ለአማራ ማኅበር በኔቫዳና ለሞገድ ዐማራ ቀስቃሾች ስብስብ ምስጋና እያቀረበ፤ ተመሳሳይ ውይይቶች ከተለያዩ የማኅበረሰባችን ክፍሎች ጋር እንደሚቀጥሉ ይገልጻል።
ድር ቢያብር፤ አንበሳ ያስር!
ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓመተ ምህረት።